ዜናፖለቲካ

ዜና: በግዜያዊ አስተዳደሩ በመቋቋም ላይ ያለው ምክር ቤት አካታች አይደለም ሲሉ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሶስት ፖለቲካ ፓርቲዎች ተቹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/2016 ዓ.ም፡- በትግራይ ክልል በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ዓረና ትግራይ ለሉአለዊነት እና ዴሞክራሲ እንዲሁም ዓሲምባ ዴሞክራስያዊ ፖርቲ በጋራ በሰጡት መግለጫ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በማቋቋም ላይ የሚገኘው አማካሪ ምክር ቤት አስመልከቶ ያጸደቀውን ውሳኔ እንደሚቃወሙት አስታወቁ።

ግዚያዊ አስተዳደሩ በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማሕበራት፣ የፀጥታ ሐይሎች እና ሌሎች አካላትን የሚያካትት አማካሪ ምክር ቤት ለማቋቋም ወስኖ አጽድቋል።

ለወራት ያክል የምክር ቤቱ ማቋቋሚያ ሰነድ በማዘጋጀት ስራው ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሶስቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤቱን ለማቋቋም ሲደረጉ የነበሩ በርካታ ውይይቶች ወደጎን በገፋ መልኩ፣ በግዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ቀርቦ የጸደቀው ሰነድ በርካታ ጉድለቶች ያሉበት ነው ሲሉ ተችተዋል፣ ለሶስት ወራት ከሁለት ሳምንታት ባካሄድነው ምክክር ወቅት ያልቀረቡ ውሳኔዎች ተካተውበታል ሲሉ ገልጸዋል።

በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንቱ እና በሁለቱ ምክትል ፕሬዝዳንቶች የተዘጋጀ ሰነድ ነው የጸደቀው ሲሉ ተችተዋል። የምክር ቤቱ ማቋቋሚያ ሰነድ እንዲያዘጋጅ የተሰየመው ኮሚቴ የማያውቀው እና እንዲገመግመው እንኳ እድል ያልተሰጠው ሰነድ ነው ቀርቦ በካቢኔው የጸደቀው ብለዋል።

የሚቋቋመው ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፍ የሚችል፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ካቢኔም የሚቆጠቀጠር፣ ህዝቡን ወክሉ በደንብ መደራደር የሚችል ተደርጎ መቋቋም አለበት በሚል አማካሪ የሚል መጠሪያ ሊሰጠው አይገባም፣ መሆን ያለበት የትግራይ ግዜያዊ ምክር ቤት ነው የሚል ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ ብናቀርብም አልተተገበረም ብለዋል።

ሌላኛው የልዩነት ሀሳብ ደግሞ የምክር ቤቱ ተጠሪነት መሆኑን አስታውቀዋል፤ ምክር ቤቱ ተጠሪነቱ አንደኛ ለህግ ማለትም ለፌደራሉ፣ የክልሉ እና አለምአቀፍ ህጎች፣ ሁለተኛ ለህሊና ሶስተኛ ደግሞ ለህዝብ ነበር ይሁን ብለን ሀሳብ ያቀረብነው፤ ነገር ግን በጸደቀው ሰነድ ተጠሪነቱ ለፕሬዝዳንቱ ተደርጓል ሲሉ አስታውቀዋል።

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢው መመረጥ ያለባቸው በምክር ቤቱ አባላት መሆን አለበት የሚል ሀሳብ ቢያቀርቡም በጸደቀው ሰነድ ላይ ግን በፕሬዝዳንቱ እንዲመረጡ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የአንድ ፓርቲ የበላይነትን በሚያስቀር መልኩ በምክር ቤቱ ላይ ሁሉም በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎቸ እኩል መቀመጫ እንዲሰጣቸው በአብላጫ ድምጽ ሀሳብ ቢቀርብም አልተተገበረም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። በካቢነው መጽደቁ በተገለጸው ምክር ቤት አጠቃላይ 105 ወንበሮች ያሉት ሲሆን ለህዌሓት 48 ወንበር ተሰጥቶታል ሌሎቹ ቀሪወን ከሌሎች ሲቪል ማህበረሰብ፣ የጸጥታ ሀይሉ እና ሌሎች ተካታቾች አካላተ ጋር እንዲካፈሉ ነው የተደረገው ብለዋል። መግለጫውን የሰጠነው ህዝቡ ምን እንደሰራን እንዲያውቅልን በሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

መግለጫውን የሰጡት ሳልሳይ ወያነ ትግራይን በመወከል የፓርቲው የህግ እና ስነመንግስት ሀላፊው የማነ ካሳ፣ የዓረና ትግራይ ለሉአለዊነት እና ዴሞክራሲ ሊቀመንበሩ አንዶም ገ/ስላሴ እንዲሁም ዓሲምባ ዴሞክራስያዊ ፖርቲ ሊቀመንበሩ ዶሪ አስገዶም ናቸው። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button