አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14/ 2015 ዓ/ም፦ ከደቡብ አትዮጵያ ክልል በኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ አካባቢ ለሚከናወን የደን ምንጣሮ በመጓዝ ላይ ሳሉ፣ በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ በፋኖ ታጣቂ ቡድን የተያዙ የቀን ሠራተኞች ከ25 ቀናት በኋላ ትላንት መለቀቃቸውን ቀጣሪ ድርጅቱ አስታወቀ።
ኒኮትካ ኮንስትራክሽንና ትሬድንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ አበበ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ እንደገለጹት 272 ሰራተኞች ተለቀው ደጀን ከተማ ደርሰዋል።
የድርጅቱ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ አለኔ የቀን ሰራተኞቹን ለማስለቀቅ በአጠቃላይ ስድስት ሚልዮን ብር ለፋኖ ታጣቂዎች መክፈሉን ገልጸዋል።
ሠራተኞቹን በቁጥጥረ ስራ ያዋልነው በመንግስት ሰራዊትነት ጥርጥረን ነው ሲሉ የገለጹት የአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ፣ ስራተኞቹን ለመልቀቅ ቡድናቸው የተቀበለው ገንዘብ የለም ሲሉ አስተባብለዋል። አክለውም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል መህበርን ሰራተኞቹን እንዲቀበላቸው ጥይቀው ነገር ግን ማህበሩ ሊቀበላቸው አለመቻሉን ገልጸዋል።
የሰራተኞቹ ቀጣሩ ድርጅት የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ አለኔ ከሰራተኞቹ መካከል አንዱ አለመገኘቱን ገልጸው “ሾልኮ እንደጠፋባቸው እና ለቤተሰብ እንደደወለ” ነው የሚነገረው ብለዋል።
ሰራተኞቹ ከደቡብ አትዮጵያ ክልል ጋርዱላ እና ኧሌ ዞን ለህዳሴ ግድብ ዛፎች ምንጣሮ ወደ አማራ ክልል መሆናቸውን የጋርዱላ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የካቲት 27/ 2016 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።
የጋርዱላ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ኩናሎ የኢትዮጵያ ኤሌክትርክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አካባቢ ለሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚፈጠርበት ቦታ ላይ ዛፎችን መቁረጥን ጨምሮ ጫካውን የመመንጠር ስራዎችን ለመከወን ጨረታ ማውጣቱን ተከትሎ ኒኮትካ ኮንስትራክሽንና ትሬድንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ ድርጅት ጨረታውን ማሸነፍፉን ሰራተኞቹን መመልመሉን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት ከደራሼ ወረዳ 246፣ ከኧሌ ዞን ደግሞ 39 የጉልበት ሰራተኞች በአንድ ላይ በ6 የድርጅቱ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ህጋዊ አካሄዶችን በመከተል ወደ አማራ ክልል በተላኩበት ውቅት ነው በፋኖ ታጣቂዎች በጥጥር ስር የዋሉት፡፡
የዞኑ አስተዳደር ምክር ቤትም “ፍፁም ንፁሃን የሆኑ ዜጎች ላይ የተፈጠረው ክስተት አሳዛኝ እና አስነዋሪ መሆኑንና ተግባሩም ያልተገባ መሆኑን” በመግለጽ ድርጊቱን በጽኑ አውግዞታል።አስ