ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ውሳኔ “ግልፅ መፈንቀለ መንግስትና የፕሪቶሪያውን ስምምነት አደጋ ላይ የጣለ ነው” ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ አጣጣለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16/ 2017 ዓ/ም፦ የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤል( ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር “በመዳከሙ” ተነስቶ በሌላ እንዲዋቀር የወሰነውን ውሳኔ እንደሚደግፉ ማሳወቃቸውን ተከትሎ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራት ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔውን “ግልፅ መፈንቀለ መንግስት እወዳ እና የፕሪቶሪያውን ውል አደጋ ላይ የሚጥል” ሲል አጣጥሏል።

ራሳቸውን የትግራይ ኃይል አመራሮች ብለው የሚጠሩት የክልሉ መኮንኖች ለቀናት ካደረጉት ስብሰባ በኋላ ትናንት ሐሙስ ጥር 15/2017 ዓ.ም. መቀለ ውስጥ በሰጡት መግለጫ የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ውሳኔ ማሳለፋቸውን አስታውቀዋል

በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊነቱን በአግባቡ አልተወጣም በማለት “የሌሎች መጠቀሚያ ሆኗል” የሚል ክስ አቅርበዋል።

በመግለጫው በጊዜያዊ አስተዳደሩ “ቁልፍ ሥልጣን የነበራቸው አመራር እና አባላት ከተሰጣቸው ተልዕኮ ውጪ የሕዝብን ጥቅም ወደ ጎን በመተው ክህደት በመፈጸም የውጭ ኃይል መሣሪያ ሆነዋል” ብሏል።

በተጨማሪም አመራሮቹ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር “ድክመቶች” ላይ የሚያተኩር እና አስተዳደሩ የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም እየሞከረ ነው በማለት ወቅሰዋል።

በዚህም ምክንያት “የተዳከመ” እና “ተልዕኮውን የዘነጋ” ያለውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማጠናከር አመራሮቹ ተነስተው በሌሎች መተካት እንዳለባቸው አሳስቧል።

ይህንን ተከትሎ መግለጫ ያወጣው የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር፤ ትናንት ጥር 15/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ስም የወጣው መግለጫ “አላማውን የሳተ እና ሰራዊቱ ከተሰጠው ተልእኮ ውጭ ነው” ሲል ከሷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“መግለጫው ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው” ሲል  የገለጸው ጊዜያዊ አስተዳደሩ “ህጋዊ ያልሆነ ቡድን ደግፎ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማፍረስ ፤ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን እና ሰራዊቱን ለመበተን መንቀሳቀስ ተቀባይነት የለውም” ሲል ገልጿል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ” ያልተለመደ ተግባር ” ሲል የገለፀውን ውሳኔ አስመልክቶ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን እና ሁኔታውን መርምሮ ዝርዝር ማብራርያ እንደሚሰጥም አስታውቋል። 

ውሳኔውን  መሬት ላይ ለማውረድ እንቅስቃሴ መኖሩን የገለጸው አስተዳደሩ፤ የሚያስከትለው አደጋው እጅግ ከፍተኛና  የህዝቡን ችግር የሚያባብስ መሆኑን በመግለጽ ተግባሩ በአስቸኳይ መቆም አለበት ሲል አሳስቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button