አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22/ 2017ዓ/ም፦ በአዲስ አበባ ከተማ በአለባበስ ምክንያት ለሁለት ሳምንት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት መደረሱን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥቅምት 20/ 2017 ዓ/ም በጻፈው ደብዳቤ፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ በሚገኙ እንዳንድ ትምህር ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያት “ጫናና እንግልት” እየደረሰ ነው ሲል ገልጿል።
በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከትምህርት ውጭ የሆኑ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱም ጥሪ አቅርቦ ነበር።
ምክር ቤቱ ትላንት ባወጣው መግለጫ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።
በተጨማሪም ጥቅምት 20/2016 መጅሊሱ ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣ የአ/አ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል ብሏል።
በዚህም ከያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው የተገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ በጊዜያዊነት ከመገለላቸው በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት ተደርሷል ሲል መጅሊሱ አስታውቋል።
ትናንት በተካሄደው 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ የምክር ቤቱ ተወካይ የሆኑት እዝታስ ካሚል ሽምሱ የሙስሊም ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዝ የተፈጠረው ችግር መፍትሄ እንዲሰጠው ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ፤ “ የአለባበስ ጉዳይ እና ሃይማኖትን በተመለከተ ችግር የለም ማለት አልችልም። ግን ትልቅ እድገት አለ፤ ከተቋማት አንጻር መሰራት ያለበት ነገር ካለ እንሰራለን” ብለዋል። አስ