አዲስ አበባ፣ ህዳር /2017 ዓ.ም፡- በትግራይ በመተግበር ላይ ያለው “ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ሂደት (DDR)ሩ እየተመራበት ያለው አካሄድ ትክክል አይደለም” ሲሉ በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ምክትል ሊቀ መንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ ገለጹ።
ባሰለፍነው አመት 2016 ዓ.ም መጨረሻ ጉባኤውን በመቀለ ከተማ በሀውልቲ አዳራሽ ያካሄደው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበር ተደርገው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ በወቅታዊ የክልሉ ጉዳይ ለጋዜጠኞች ትላንት ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ማብራርያ ሰጥተዋል።
አቶ አማኑኤል የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ መልሶ በማቋቋም እና ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል (DDR) ሂደት አስመልክተው በጋዜጣዊ መግለጫቸው በሰጡት አስተያየት ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ሂደት (DDR)ሩ “በፕሪቶሪያ ስምምነት እንደ ቅድመሁኔታ የተቀመጠ ነው” ሲሉ ገልጸው በትግራይ ግዛቶች “ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ታጣቂ ሃይሎች ሲወጡ ይፈፀማል” ነው የሚለው ሲሉ አስታውቀዋል።
ይህን መሰረት ያደረገ DDR ህወሓት የተስማማበት ስለሆነ ተቃርኖ የለውም ያሉት አቶ አማኑኤል በዚህ ሰሞን እየተፈፀመ ያለው ዲዲኣር በዚህ መልክ መሆን ነበረበት፣ በአጠቃላይ ዲዲአሩ እየተመራበት ያለው አካሄድ ግን ትክክል አይደለም ሲሉ ተችተዋል።
ለመቋቋሚያ ተብሎ እሚሰጠው ማነሱ ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት ሂወታቸውን እንዴት ሊመሩ ይችላሉ የሚለው እቅድ ወጥቶለት መመራት አለበት ሲሉ የገለጹት አማኑኤል አሰፋ ከባዮሜትሪክ ዳታ አሰባሰብ ጋር ተያይዞም ግልፅነት የጎደላቸው ኣካሄዶች አሉ፤ እነዚህን በሚፍታና ህይወታቸውን በዘላቂነት በሚያመቻች ሁኔታ ነው መሰራት ያለበት ሲሉ አሳስበዋል።
“ከፕሪቶሪያ ስምምነት አግባብ ውጭ በሆነ መንገድ ጊዚያዊ መስተዳድሩ በግለሰቦች እጅ ወድቋል” ያሉት አቶ አማኑኤል “ስምምነቱ እየተፈፀመ አይደለም ብለን ገምግመናል” ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አንጸባርቀዋል።
በግዚያዊ መስተተዳድሩ አመራር ላይ ያለው የህወሓት ድርሻን በሚመለከትም ድርጅታዊ ጉባኤ ኣካሂደን ከገባንበት ችግር ለመውጣት የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ኣውጥተን ውሳኔ አሳልፈናል ሲሉ ተናግረዋል።
በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ያለው አመራር ለሁለት አመት ያለምንም እቅድ ነው ጊዚያዊ መስተዳድሩን የመራው ሲሉ የተቹት አቶ አማኑኤል “ሁለት አመት ሙሉ ትግራይን እሚመራበት ግልፅ እቅድ አልነበረውም፣ በጭፍን አይን ነው የተጓዘው ሲሉ ተችተዋል።
ተቆጥረው የተሰጡትን ተልእኮዎች አልፈፀመም ብቻ ሳይሆን በተቃራኒ ነው የሚሰራው ያሉት አማኑኤል አሰፋ ተልእኮዎቹ ሰላምና ፀጥታ ማስከበር፣ ክልሉ እንዲያገግም ማድረግና ዳግመ ግንባታ ማረጋገጥ፣ የፕሪቶሪያን ስምምነት ማስተግበር፣ ፍትሕና የህግ ልዕልና ከነ የጀኖሳይድ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ እና በህዝብ የሚመረጥ መንግስት እንዲቋቋም ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይሚሉ ናቸው ሲሉ ዘርዝረዋል።
“ሆኖም ግን ግዚያዊ መስተዳድሩ እነዚህ ተቆጥረው የተሰጡትን ስራዎች አልሰራቸውም” ሲሉ ተደምጠዋል።
ጊዚያዊ መስተዳድሩ የተሰጡትን ሃላፊነቶች ትቶ “ህወሓትን ለማፍረስ ወይም ለማዳቀል ነው ሲሰራ እሚውለው” ሲሉ የተደመጡት አቶ አማኑኤል ሰራዊት ተቆጣትሮም ወታደራዊ አገዛዝ ለመመስረት ተንቀሳቅሷል” ሲሉ ገልጸዋል። አስ