ህግ እና ፍትህዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26/ 2017 ዓ/ም፦ ከአንድ አመት እስር በኋላ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመውጣት ላይ እያሉ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎት ተይዘው ወደ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተወሰዱት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቀሉ።

“አቶ ታዬ ስልክ ደውለው ወጥቻለው ኑ ውሰዱኝ” ማለታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። ከዚያም በቅርብ አካባቢ የሚገኝ የቤተሰብ አባል ወደ ቤት እንደወሰዷቸው አክለው ገልጸዋል።

አቶ ታዬ ደንዳኣ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ትናንት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመውጣት ላይ እያሉ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎት ከበር ላይ ተይዘው ወደ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸውን አዲስ ስታንዳርድ ቀደም ሲል ዘግቧል

አቶ ታዬ ህዳር 23 ቀን በዋለው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስትና እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ነው ትላንት ህዳር 25፣ 2016 ዓ/ም ከእስር ቤት እንደተለቀቁ ከበር ላይ “ምስክ ባደረጉ” ሰዎች መወሰዳቸው የተገለጸው። 

ባለቤታቸው አቶ ታዬ ዛሬ ህዳር 26 ቀን  ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸውን ተናግረዋል።

የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደኣ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ታህሳስ 2 ቀን በጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። 

አቶ ታዬ ደንደኣ  ታኅሣስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋሉት  “ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረሰላም ኃይሎች ጋር በመተሳሰር  ለጥፋት ተልዕኮ በህቡዕ ሲሰሩ ስለተደረሰባቸው” በሚል መሆኑን የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብረ ኃይል በወቅቱ አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሐምሌ 30 በዋለው ችሎት ከቀረቡባቸው ሦስት ክሶች መካከል በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ነጻ የተባሉ ሲሆን የጦር መሳሪያ ወንጀሎችን በተመለከተ የቀረበባቸውን ሶስተኛው ክስ እንዲከላከሉ ብይን መሰጠቱም ይታወሳል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button