አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም፡- አለምአቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ ትላንት ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ በተያዩ አከባቢዎች በመካሄድ ላይ ባሉ ግጭቶች፣ መፈናቀሎች እና የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ከዘጠኝ ሚሊየን በላይ ህጻናት በትምህርት ገበታ ላይ እንደማይገኙ አስታወቀ።
ከስድስት ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል ያለው ሪፖርቱ በተጨማሪም ከ10 ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች በግጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ጉዳት ደርሶባቸዋል ወድመዋል ሲል ገልጿል፤ ይህም የመማር ማስተማሩ ሂደት ሰላማዊ እና ተደራሽ እንዳይሆን አስተዋጽኦ ማድረጉን አመላክቷል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህጻናት ወደ ትምህርት ገበታ ያልሄዱት በአማራ ክልል መሆኑን አስታውቋል 4 ነጥብ አራት ሚሊየን ህጻናት ትምህርት ቤት አለመሄዳቸውን ጠቁሟል።
በሁለተኛ ደረጃ የኦሮምያ ክልል ህጻናት ወደ ትምህርት ገበታ አለመሄዳቸውን የጠቆመው የዩኒሴፍ ሪፖርት 3 ነጥብ 2 ሚሊየን የኦሮምያ ህጻናት ትምህርት ቤት አለመሄዳቸውን አመላክቷል። በሶስተኝነት የትግራይ ክልል መሆኑን የጠቆመውሪፖርቱ አንድ ነጥብ 2 ሚሊየን የትግራይ ህጻናት ወደ ትምህርት ገበታ አለመሄዳቸውነ አስታውቋል።
“በአማራ ክልል 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምሕርት ቤት አልሄዱም” ሲሉ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅት እና አጀማመርን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት መግለጻቸው ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም መዘገባችን ይታወሳል።
በአማራ ክልል አንድም ትምህርት ቤት ያልተከፈተባቸው 17 ወረዳዎች መኖራቸውን እና እንደ ክልልም 40 በመቶ ምዝገባ ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶች መኖራቸው መግለጻቸውም በዘገባው ተካቷል።
ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ 7 ሚሊዮን 71 ሺህ 933 ተማሪ ለመመዝገብ ታቅዶ የተመዘገበው 2 ሚሊየን 543 ሺህ 128 መኾኑን ማስታወቃቸውም ተካቷል።
በሰሜኑ ጦርነት ከወደሙ 4 ሺህ ትምህርት ቤቶች መካከል የተጠገኑት ከ10 በመቶ በላይ ስላልኾኑ በጥራት ላይ ችግር እንዳለውም መግለጻቸውም ይታወቃል። አስ