ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና: "ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ አወንታዊ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ከአማኙ ጋር በመመካከር ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል" - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም፡- በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት እንዳይከታተሉ መከልከሉን ተከትሎ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ “ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ከአማኙ ጋር በመመካከር ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል” ሲል አስጠነቀቀ።

ምክር ቤቱ ባወጣው ባለ 11 ነጥብ አቋም መግለጫ “የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ አስመልክቶ ያወጣው ህግ እንዲከበር እንጠይቃለን” ብሏል።

ምክር ቤቱ “ሒጃቧንም ታደርጋለች ትምህርቷንም ትማራለች” በሚል መሪ ሀሳብ በሰጠው መግለጫ “ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወስዳለን” ሲልም ገልጿል።

ትግራይ ያለችበት ፖለቲካዊ እና ከባቢያዊ ቀውስ በቂ ነው ያለው መግለጫው ሌላ ሃይማኖትን መሠረት ላደረገ የቀውስ በር መክፈት ክልሉ ከድጡ ወደ ማጡ መክተት ነው ሲል አሳስቧል።

በጦርነት ምክንያት ለሶስት አመታት ከትምህርት ርቀው የነበሩ ሙስሊም ሴት ተማሪዎቻችን ማገዝ ሲገባ ማንነታቸውን የሚያንፀባርቅ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከትምህርት ገበታ እንዲርቁ ማድረግ ህገወጥ እና ኢፍትሃዊ ነው” ሲል ኮንኗል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት እንዳይከታተሉ መከልከሉን በተመለከተ ምንም እልባት አለመገኘቱን ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም መዘገባችን ይታወሳል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በመግለጫው “የአክሱም ከተማ ትምህርት ቢሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን የእምነት አለባበስ አስመልክቶ ትምህርታቸውን በሚጎዳ መልኩ ከአንድ ወር ባላነሰ ጊዜ ከትምህርት ገበታቸው እንዲስተጓጎሉ ከማድረጉም ባሻገር አንዳንድ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው መታሰራቸውን” ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የአክሱም ከተማ የእስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ሐሙስ መስከረም 30/ 2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ በአራት ትምህርት ቤቶች ማለትም ወረ፣ ክንዴያ፣ አደባባይ እና መሰናዶ የሚማሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ወደ 140 የሚጠጉ ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና ምዝገባ መከልከላቸውን መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button