ማህበራዊ ጉዳይዜናፖለቲካ

ዜና: ተመሳሳይ ይዘት ባለውና ዝርዝር ምክንያት ባልተገለጸበት ሁኔታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ እየተጣለ ያለው እግድ አሳስቦኛል - ኢሰመኮ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም፡- የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው በሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ እያሳለፈው ያለው የእግድ ውሳኔ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።

ኢሰመኮ ዛሬ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከቅብር ግዜያት ወዲህ በበርካታ የሲቪል ተቋማት ላይ እግድ እየጣለ እንደሚገኝ አስታውቆ ለተቋማቱ መታገድ እየቀረበ ያለው ምክንያት ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው፣ በዝርዝር የተገለጸ ነገርም የለውም ሲል ተችቷል።

“ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የሀገርን ጥቅም የሚጎዳ ተግባራት ላይ መሰማራቱ” የሚል ተመሳሳይ ይዘት ያለው የእገዳ ደብዳቤ ነው የደረሳቸው ሲል ጠቁሟል።

“ተቋሟቱ የፈጸሟቸውን ከባድ የሕግ ጥሰቶች በዝርዝር ባላስቀመጠ ደብዳቤ መታገዳቸው አሳሳቢ ሆኖ” አግኝቸዋለሁ ብሏል።

በተያዘው ወር ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እግድ የተጣለባቸው በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አራት ደርሰዋል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚተላለፉ ተደጋጋሚ እገዳዎች የሲቪክ ምኅዳሩን በማጥበብ በማኅበር የመደራጀት መብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያሳድር ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ባለሥልጣኑ የድርጅቶቹን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ የምርመራ ሥራዎቹን በተቻለ ፍጥነት አጠናቆ ወደ ሥራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) “ገለልተኛ ባለመሆን ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል  ምክንያት ማገዱ የተመለከተ ዘገባ ትላንት ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ማውጣታችን ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC) ከባለሥልጣኑ ታኅሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በተላከለት ደብዳቤ መታገዱን ትላንት ታህሳስ 17 ቀን ያወጣውን አስቸኳይ መግለጫ ዋቢ በማድረግ በዘጋችን ተካቷል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን መታገዱንም የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘገባን ዋቢ በማድረግ በዘገባው ተመላክቷል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከልን (ካርድ) ጨምሮ በሶስት አገር በቀል ሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ላይ ጥሎ የነበረውን  ዕግድ ማንሳቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ባለስለጣኑ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በጻፈው እና ለተቋሙ ትላንት ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በደረሰው ደብዳቤ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከልን (ካርድ) በድጋሚ መታገዱን በተቋሙ የሚሰሩ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።

ካርድ በድጋሚ ለመታገድ ያደረሰው ምክንያት ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረው እገዳ ሲነሳ “የተገለጸለትን የእርምት እርምጃዎች ባለመውሰድ“እንዲሁም “ለተሰጠው ማስጠንቀቂያ ትኩረት መንፈግ” የሚል መሆኑን ምንጫችን አመላክተው ነበር። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button