ዜናፖለቲካ

ዜና: የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት በይፋ ተቋቁሞ ስራ ጀመረ፣ የዲያስፖራ እና የጸጥታ አካላት አልተሳተፉበትም ተብሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 26/2017 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር አማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሙና በይፋ ስራ መጀመሩን አስታወቀ። ጊዜያዊ አስተዳደሩ አቶ ሞገስ ታፈረን የምክር ቤቱ ዋና ሰብሳቢ አድርጎ የመረጠ ሲሆን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ነጻነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆኑትነ ደጀን መዝገቦን (ዶ/ር) ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ መምረጡ ተገልጿል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ከሲቪል ማህበራት፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ዲያስፖራ፣ የክልሉ ሙሁራን እና የጸጥታ አካላት ተወካዮችን ያካተተ እንደሚሆን ተገልጿል።

ትላንት በተቋቋመው የአማካሪ ምክር ቤቱ ወስጥ ግን የክልሉ የጸጥታ አካላት፣ ሳልሳይ ወያነ ፖለቲካ ፓርቲ፣ የክልሉ ዲያስፖራ አባላት ተወካዮች አለመሳተፋቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ባቀረበው ዘገባ አስታውቋል።

በቀጣይ እንዲሳቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በአማካሪ ምክር ቤቱ ምስረታ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ቢሮዎችን አፈጻጸም የሚከታተል እና የሚደግፍ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱና ሁኔታዎች ምክር ወይም ውሳኔ የሚያሳልፍ አማካሪ ምክር ቤት መመስረት የሚያስፈልግበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

“ልዩነቶቻችንን እንደ ነውር ሳይሆን እንደልሙድ አሰራር በመቁጠር፤ ልዩነቶቻችን ላይ ሳይሆን አንድ የሚያደርጉን እና የወደፊት ህልውናችንን በሚያረጋግጡልን ጉዳዮች ላይ መስራት አለብን” ሲሉ አሳስበዋል።

የግዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የአስተዳደራቸውን ቀጣይ ስድስት ወራት ዕቅድ ለተመሰረተው አማካሪ ምክር ቤት አቅርበው ማስገምገማቸውም ተጠቁሟል። አቶ ጌታቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ቀጣይ ስድስት ወራት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ የክልሉ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ ነው ሲሉ አስታውቀዋል። ይህንንም ለማስፈጸም የሁሉም እገዛ ያስፈልጋል ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ለአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት በአቶ ጌታቸው ረዳ የቀረበው የጊዜያዊ አሰተዳደሩ የቀጣይ ስድስት ወራት ዕቅድ ያለምንም ተቃውሞ በስምንት ድምጸ ተአቅቦ መጽደቁን ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በምርጫ ቦርድ እወቅና ተሰጥቶት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሚያቋቁመው የአማካሪ ምክር ቤት እንደማይሳተፍ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

ፓርቲው በመግለጫው የአማካሪ መክር ቤቱን ለማቋቋም በሚል ተሰይሞ የነበረው ኮሚቴ ካቀረበው ምክር ሃሳብ ባፈነገጠ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የማቋቋሚያ ደንቦቹን ለራሱ በሚያመቸው መንገድ በመተካት እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል መኮነኑም በዘገባው ተካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button