ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የትግራይ ሊሂቃን የህዝቡን አንድነት በሚያረጋግጥ መልኩ ልዩነቶቻቸውን በሰላምና በውይይት እንዲፈቱ ጠ/ሚንስትሩ ጠየቁ

ዜና፡ የትግራይ ሊሂቃን የህዝቡን አንድነት በሚያረጋግጥ መልኩ ልዩነቶቻቸውን በሰላምና በውይይት እንዲፈቱ ጠ/ሚንስትሩ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27/2017 ዓ.ም፡- ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የትግራይ ህዝብ አሁንም ሰላምና መረጋጋት አግኝቶ ሰርቶ እንዳይገባና እንዳይለማ “በጦርነት ወሬ፣ ፍርሃት፣ ሽብር እየኖረ ነው” ሲሉ ገለጸው የትግራይ ልሂቃን ልዩነቶቻችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጠየቁ።

ጠ/ሚኒስትሩ አብይ ትላንት ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ለትግራይ ህዝብ በተለይ ለትግራይ ሊሂቃን ሲሉ ባቀረቡት ጥሪ የክልሉ ህዝብ በተደጋጋሚ ጦርነቶ ተጎጂ እንደነበር በመጥቀስ ህዝቡ ወደ ልማትና ማገገም እንዲመለስ አብረን እንስራ ብለዋል።

በፖለቲካ፣ በቢዝነስ፣ በፀጥታ ፣ በአካዳሚክ እና በሚዲያ እና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ የትግራይ ተወላጆች “ህዝብ እስካሁን የተከፈለው ዋጋ ይበቃዋል፣ ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም ብላችሁ” እንድትንቀሳቀሱ ሲሉ ምክረ ሃሳባቸውን አቅርበዋል።

በውስጣችሁ ያለው ልዩነት “በሰላም በውይይትና በመረዳዳት የትግራይ ህዝብ አንድነት በሚያረጋግጥ መንገድ ጉዳያችሁ እንድትጨርሱ” ሲሉ ጠይቀዋል።

በአብዘሃኛው መልዕክታቸው የትግራይን ህዝብ በሀገረ መንግስቱ ምስረታ ያወደሱት ጠ/ሚኒስትሩ “በተለያዩ ዘመናት ማዕከላዊ መንግስት እንቅፋት ሲገጥመው ሀገሪቱን በማዳን እና ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል” ብለዋል።

ለዘመናት የትግራይ ህዝብ በጦርነት ማሳለፉን ያወሱት ጠ/ሚኒስትር አብይ በተለይም ግን ባለፉት መቶ አመታት ከማዕከላዊ መንግስቱ ጋር በተለያዩ አጋጣሚዎችን እና ምክንያቶች ግጭቶች ውስጥ መግባቱን በማስታወስ ጉዳት ማስተናገዱን አመላክተዋል፤ “የትግራይ መሬት የጦር አውድማ ሆኗል፤ የትግራይ ህዝብም የጦርነት መጠቀሚያ ሆኗል” ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በመሆኑም የክልሉ ልሂቃን “ትግራይና ህዝቦቿ ከጦርነቱ ያገኙት ወይስ ያጡት ጥቅም ይበዛል ብሎ መጠየቅና መልስ ማግኘት አለበት” ሲሉ አሳስበዋል።

ከፌደራል መንግስትና ከሌሎች ሃይሎች ጋር ያላችሁን አለመግባባት በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ እንድትሆኑ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በፌዴራል መንግሥት በኩል በሁሉም ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ዝግጁ ነው ሲሉ አስታውቀዋል፤ “በተግባባንባቸው አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተስማምተን እንድንሠራ የሚያደርግ ሁኔታ መኖሩን እንድትገነዘቡ ሲሉ በመልዕክታቸው አሳስበዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ “ህዝብን ከስጋት፣ እናቶች እንቅልፍ ከማጣት፣ ወጣቶች ከመሰደት ማዳን ላይ እንድትሰሩ ሲሉም አሳስበዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button