ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና: ፍርድ ቤቱ የሂጃብ እገዳ እንዲቆም ያሳለፈውን ውሳኔ ያልተቀበሉ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ አዘዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20/ 2017 ዓ/ም፦ የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የሚከለክለውን መመሪያ በማገድ ያስተላለፈውን ውሳኔ ያልተቀበሉ የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ አዘዘ።

ፍርድ ቤቱ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው የእስር ማዘዣ ከ2ኛ እስከ 5ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች “የፍርድ ቤቱን ግልፅና ህጋዊ ሥርዓት ሆን ብለው በመጣስ” የፈጸሙት ድርጊት “የፍርድ ቤቱን ስልጣን የሚያዳክም ነው” በማለት ከሷል።

የወረዳ ፍርድ ቤቱ በማዛዣ ደብዳቤው  የፍትሃብሄር ህጉን አንቀጽ 156 (1) በመጥቀስ በፍትሐብሔር ክርክር ውስጥ ያለ ማንኛውም ተከሳሽ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ ያላከበረ እና የጣሰ እንደሆነ አግባብነት ባለው የወንጀል ሕጉ ድንጋጌ ተጠያቂ እንደሚሆን አመልክቷል።

በዚህም የተከሳሾች አስተዳደራዊ ትእዛዝ ወይም ውሳኔ ይህ መዝገብ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ በጊዜያዊነት ታግዶ እንዲቆይ አዟል።

የተከሳሾቹ ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ-154 መሰረት ታግዶ ካልቆየ በእስልምና እምነት ተማሪዎች ላይ የማይመለስ የሰብአዊ እና የሞራል ጥሰቶች እና እንግልት እንደሚያስከትል ፍርድ ቤቱ አመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የሚከለክለውን የትምህርት ቤት መመሪያ በማገድ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰጠው መመሪያ በኋላ የተላለፈው ውሳኔ “የማይቀለበስ የመብት ጥሰት” ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ጠቅሷል።

በወቅቱ አምስት ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት እንዳይከታተሉ በመከልከላቸው ለተሰነዘረባቸው ክስ ምላሽ እንዲሰጡ ተጠርተዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በበኩሉ ቅሬታውን ገልፆ ትምህርት ቤቶቹ የሙስሊም ተማሪዎችን ህገ-መንግስታዊ የሆነውን የትምህርት እና የሃይማኖት ነፃነት መብቶችን ጥሰዋል በማለት ክስ አቅርቧል።

ጉዳዩ በአክሱም ከተማ በሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች መካከል ተቃውሞ ያስከተለ ሲሆን ተማሪዎቹ እገዳው የሃይማኖት እና የትምህርት ነፃነታቸውን የሚጋፋ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎ በአክሱም ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሂጃብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የታደሙበት ሰልፍ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀለ ከተማ አካሄደዋል።

ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሂጃብ ለመልበስ የሚያስችላቸውን መብት ያረጋግጣሉ የተባሉትን የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ መመሪያዎችን በመተግበር ረገድ እየታዩ ናቸው ያሏቸውን መለሳለስ በመቃወም ሰልፈኞቹ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ከ2ኛ እስከ 5ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾች ርዕሰ መምህራንን የካቲት 07/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ላይ በእስር አጅቦ ወደ ፍርድ ቤት እንዲያቀርባቸው መመሪያ አስተላልፏል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button