![](wp-content/uploads/2025/01/IMF-1024x682-1-1024x645.jpeg)
አዲስ አበባ፣ ጥር 22/2017 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ ገቢን ለማሳደግ በሚል እያከናወነች ያለችው የግብ ማሻሻያ እርመጃዎቿ በታሰበው ልክ እየሄደ ይገኛል ሲል አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) አወደሰ።
የገንዘብ ተቋሙ ትላንት ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው ኢትዮጵያን የተመለከተ ያካሄደው ግምገማ ሪፖርት እንደሚያሳየው መንግስት ገቢዎቹን ለማሳደግ፣ የገቢ ክፍተቶቹን ለሞሙላት በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብሏል።
መንግስት ወስብስብ እና ማነቆ የነበሩ የግብር ሁኔታዎችን በማሰተካከል ላይ እንደሚገኝም ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ መንግስት በማንፋክቸሪን ዘርፍ ለተሰማሩ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሃብቶች ሰጥቶት የነበረውን ከቀረጽ ነጻ ግብአት የማስገባት እድሎችን በማስቀረት፣ ግብር እነዲከፍሉ የሚያደርገ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን አይ ኤም ኤፍ በሪፖርቱ አመላክቷል።
ሪፖርቱ በተጨማሪም የግብር ፖሊሲዎቹ ላይ ባካሄደው ምዘናዎች “በታቀደው መሰረት እየሄዱ ናቸው” ሲል በመግለጽ “በኮርፖሬሽኖች ላይ የሚታየውን የገቢ ታክስ ስርዓት ክፍተቶችን ለመሙላት” እንዲሁም “አነስተኛ እና ኢመደበኛ ንግዶችን ወደ መደበኛ የግብር ስርአት ለማስገባት” ትኩረት መደረጉን አስታውቋል።
የገንዘብ ተቋሙ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርቱ የሀገሪቱ አጠቃላይ ግሽበት በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም ከሐምሌ ወር በኋላ 25 በመቶ ይደርሳል ሲል አሳስቧል። ወደ አንድ አሃዝ ዝቅ ሊል የሚችለው ከሶስት አመታት በኋላ ነው ሲል ትንበያውነ አስቀምጧል።
በተያያዘ አለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ በ48 ወራት ውስጥ በብድር ሊሰጥ ካቀደው 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ውስጥ ሁለተኛውን 248 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማጽደቁን በሪፖርቱ አስታውቋል።
የገንዘብ ተቋሙ ለኢትዮጵያ የተራዘመ ብድር ለመስጠት ውሳኔ ያሳለፈው በያዝነው አመት መጀመሪያ መስከረም ላይ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ግምገማው 345 ሚሊዮን ዶላር መልቀቁ ይታወሳል።
አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በአራት አመታት የተራዘመ ብድር ለኢትዮጵያ ለመስጠት ከፈቀደው የ3.4 ቢሊየን ዶላር ውስጥ ሁለተኛው ዙር የ250 ሚሊየን ዶላር ብድር እንዲለቀቅ የሚያስችል ግምገማን ማጽደቁን የተመለከተ ዘገባ ጥር 10 1ን 2017 ዓ.ም ማቅረባችን ይታወሳል።
ትላንት ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም የገንዘብ ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 248 ሚሊየን ዶላር ብደር አጸድቋል ብሏል።
ትላንት የተለቀቀወ ጨምሮ አይኤምኤፍ አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊየን ዶላር ለኢትዮጵያ በተራዘመ ብድር መስጠቱን በመግለጫው አመላክቷል።
ብድሩ የተለቀቀው ሀገሪቱ በማከናወን ላይ ላለችው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማስፈጸሚያ ነው ሲል ተቋሙ በመግለጫው አትቷል። አስ