አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22/ 2017 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ በቡግና እና ላስታ ወረዳ “በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ” በተጠሉ ገደቦች ምክንያት ቀድሞውኑ አስከፊ የሆነውን የሰብአዊ ሁኔታ በማማባስ 10 ሺህ ተፈናቃዮችን ጨምሮ 77 ሺህ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ማድረሱን የአውሮፓ ሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ እርዳታ ኦፕሬሽንስ (ECHO) ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።
ሪፖርቱ “የቴሌኮሙኒኬሽን እና ባንክ አገልግሎቶች ስራ ላይ አለመሆናቸውንና የመንግስት መዋቅሮችም ለሶስት ወራት በስፍራው እንዳልነበሩ” ገልጿል። በተጨማሪም “የሰብአዊ እርዳታ እጥረት እና ዝቅተኛ የሰብል ምርት እንዲሁም ከፍተኛ የምግብ ዋጋ፤ የምግብ ዋስትና እጦት እንዲባባስ አድርገዋል” ብሏል።
79 በመቶ የሚሆኑ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች እንዲሁም 70 በመቶ የሚሆኑ ሕፃናት ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳለባቸው የገለጸው ሪፖርቱ ከዚህ ውስጥ 9 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ደግሞ እጅግ ከባድ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አለባቸው ገልጿል። ጤና ተግዳሮቶችን በተመለከተም 5,747 ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን እና የእከክ በሽታ እየጨመረ” መሆኑን ተልጿል።
በተጨማሪም 77% የሚሆኑት ነዋሪዎች የንጹህ ውሃ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው ሲሆን መደበኛ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ዕድሜያቸው ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የደረሰ ተማሪዎች 35 በመቶ ብቻ ናቸው ተብሏል።
“በዓለም ምግብ ፕሮግራም እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኩል የአኘት ምግብ ድጋፍ ማከፋፋል ተጀምሯል” ያለው ሪፖርቱ አክሎም፤ በአውሮፓ ሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ እርዳታ ኦፕሬሽኖች የገንዘብ ድጋፍ በተደረገ ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ሂደት አስቸኳይ የተመጣጠነ ምግብ፣ የውሃ እና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ ለመስጠት ተችሏል።
በአማራ ክልል በመንግስት ሃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ግጭት እየተባባሰ በመምጣቱ የሲቪል ህይወት መጥፋት፣ ትምህርት ቤቶች በስፋት መዘጋትን እና የእርዳታ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል አስከትሏል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ቀደም ሲል በቡግና ወረዳ ያሉ የፀጥታ ችግሮች “የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነትን እንዳደናቀፉ” ገልጸዋል። ነገር ግን መንግስት ቀውሱን ለመቅረፍ “በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ክምችትና ዝግጅት” እንዳሉት አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር በጸጥታ ችግር ምክንያት ላለፉት ሁለት ወራት ማድረስ ያልተቻለው እርዳታ በሀገር ሽማግሌዎች ስምምነት መደረጉን ተከት መጓጓዝ መጀመሩን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ቀውስ የሚገልጹ ሪፖርቶችን እየተከታተለ መሆኑን ትናንት ታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። “የኢትዮጵያ ህዝብን ለመደገፍ አጋሮቻችን ምግብ እና አልሚ ምግቦችን ወደተጠቁት ስፍራዎች እየላኩ ነው” ያለው ኤምባሲው ሁኔታውን በቀጣይም በመከታተል ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ጠቁሟል።አስ