አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30/ 2017 ዓ.ም፦ የአማራ ክልል መንግሥት ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በድርቅ እና በግጭት ለተጎዱ ዜጎች የሚያደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማገዝ ዝግጁ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አረጋገጡ፡፡
ትናንት ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ልዑካን ጋር ሁሉን አቀፍ ሰብዓዊ ድጋፎች ተደራሽ ስለሚኾኑበት እና ከክልሉ መንግሥት ጋር በትብብር ስለሚሠሩበት ሁኔታ መነጋገራቸውን ገልጸዋል።
ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በአማራ ክልል የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ልዑካን መሪ ብሩስ ቢቨር ማረጋገጣቸውን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ የሻምበል ዋለ በበኩላቸው ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ አገልግሎት ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ እና መጠን ተደራሽ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በቀጣይም በክልሉ ከሚመለከታቸው የክልል ቢሮ ኀላፊዎች ጋር ተጨማሪ ውይይቶችን በማድረግ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገቡም ተናግረዋል ተብሏል፡፡
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በ16 ቀበሌዎች በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሳቢያ በተከሰተ የምግብ ዕጥረት 110 ሺህ ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል።
አልሚ ምግብና በመድሀኒት አቅርቦት ችግር ምክንያት ጉዳት መደረሱንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ከቡግና ወረዳ በተጨማሪም በላስታ ዙርያ ወረዳዎች የምግብ እጥረት መከሰቱ የተገለጸ ሲሆን በአካባቢዎቹ በመንግሥት የጸጥታ አካላት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተከሰተው ግጭት ምክንያት አስፈላጊውን እርዳታ በወቅቱ ማስገባት አለመቻሉን የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል፡፡
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በህጻናት መቀንጨርና በምግብ እጥረት ለተጎዱ ከ110 ሺህ በላይ ሰዎች ከሁለት ወራት በኋላ የርዳታ እህል መጓጓዝ መጀመሩንም ዐክለው ተናግረዋል።
እርዳታው መጓጓዝ የጀመረው በጸጥታ ችግር ምክንያት ላለፉት ሁለት ወራት እርዳታ መድረስ ባለመቻሉ በሀገር ሽማግሌዎች ስምምነት መደረጉን ተከትሎ መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
የአውሮፓ ሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ እርዳታ ኦፕሬሽንስ (ECHO) ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በክልሉ ሰሜን ወሎ በቡግና እና ላስታ ወረዳ “በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ” በተጠሉ ገደቦች ምክንያት ቀድሞውኑ አስከፊ የሆነውን የሰብአዊ ሁኔታ በማማባስ 10 ሺህ ተፈናቃዮችን ጨምሮ 77 ሺህ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ማድረሱን አስታውቋል።
ሪፖርቱ “የቴሌኮሙኒኬሽን እና ባንክ አገልግሎቶች ስራ ላይ አለመሆናቸውንና የመንግስት መዋቅሮችም ለሶስት ወራት በስፍራው እንዳልነበሩ” ገልጿል። በተጨማሪም “የሰብአዊ እርዳታ እጥረት እና ዝቅተኛ የሰብል ምርት እንዲሁም ከፍተኛ የምግብ ዋጋ፤ የምግብ ዋስትና እጦት እንዲባባስ አድርገዋል” ብሏል።
79 በመቶ የሚሆኑ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች እንዲሁም 70 በመቶ የሚሆኑ ሕፃናት ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳለባቸው የገለጸው ሪፖርቱ ከዚህ ውስጥ 9 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ደግሞ እጅግ ከባድ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አለባቸው ገልጿል። ጤና ተግዳሮቶችን በተመለከተም 5,747 ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን እና የእከክ በሽታ እየጨመረ” መሆኑን ተልጿል።
በተጨማሪም 77% የሚሆኑት ነዋሪዎች የንጹህ ውሃ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው ሲሆን መደበኛ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ዕድሜያቸው ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የደረሰ ተማሪዎች 35 በመቶ ብቻ ናቸው ተብሏል። አስ